Presentation is loading. Please wait.

Presentation is loading. Please wait.

የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ት/ቤት ደህንነት እና ሰላም የሚቀርብ ገለፃ

Similar presentations


Presentation on theme: "የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ት/ቤት ደህንነት እና ሰላም የሚቀርብ ገለፃ"— Presentation transcript:

1 የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ት/ቤት ደህንነት እና ሰላም የሚቀርብ ገለፃ
ፌብሩወሪ 27፣ 2018

2 የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ጓዶች በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በደህንነት ጥበቃ የሚረዱ ጓዶች ተመድበዋል።
የደህንነት ጥበቃ ቡድን መሪዎች በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከመመደባቸውም በላይ አብዛኛውን ጊዜ ከመጋቢ ት/ቤቶችም ጋር ይሠራሉ። የት/ቤት መገልገያና-ንብረት ኃላፊዎች የሚመደቡት በሞንጎመሪ ካውንቲ የፖሊስ ዲፓርትመንት (MCPD) ሲሆን በቀጥታ ከተመደቡበት ት/ቤት ጋር ይሰራሉ። እንደየአስፈላጊነቱ ከመጋቢ ት/ቤቶችም ጋር በትብብር እና በምክክር ይሰራሉ። የኤለመንተሪ ት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ጓድ የሚያካትተው የት/ቤት አስተዳዳር እና መምህራንን ሲሆን በሥፍራው ለድንገተኛ (OSET) ሁኔታ ዝግጁ የሆነ ቡድን ነው። በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ክልል/cluster ውስጥ የሚገኙ የደህንነት ጥበቃ ጓድ አባላት እና SRO አሳሳቢ/ከባድ ሁኔታዎች ሲከሰቱ ከኤለመንተሪ ት/ቤት አስተዳደር ጋር በመተባበር የድንገተኛ ሁኔታ ክስተት እና ምላሽ እቅድ ላይ ይሳተፋሉ።

3 የዋናው ጽ/ቤት ማእከል የደህንነት ጥበቃ ስምሪት
የክልል/Cluster ደህንነት ጥበቃ አስተባባሪዎች በድንገት ለሚከሰቱ የደህንነት ሁኔታዎች የልምምድ እንቅስቃሴዎችን/safety drills እና በት/ቤት ስጋት የሚያስከትሉ ጉዳዮችን በሚመለከት የት/ቤት አስተዳዳሪዎችን እና የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ጓዶችን ያማክራሉ። አስተባባሪዎቹ አሳሳቢ ከባድ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ምላሽ በመስጠት ወይም በት/ቤትና በት/ቤት ማህበረሰብ መካከል ምርመራዎች ሲኖሩ አስተያየቶችን በመስጠት፣ መመሪያ፣ እና ለት/ቤት አስተዳደር ለኤለመንተሪ ት/ቤት የድጋፍ ምንጭ በመሆን ይሰራሉ የደህንነት ተቆጣጣሪዎች በኤሌክትሮኒክስ ፍተሻ ክፍል በምሽት እና በሣምንት መጨረሻ ቀናት ት/ቤቶችን እና ሌሎች የ MCPS ንብረት በመቆጣጠር ይሰራሉ።

4 ት/ቤትን መሠረት ያደረገ የደህንነት ጥበቃ ስምሪት በቁጥር
የደህንነት ጥበቃ ሚና ጠቅላላ የሠራተኛ ቁጥር የደህንነት ጥበቃ ድጋፍ ሰጪዎች 200 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት = 123 መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት = 77 የደህንነት ጥበቃ ጓድ መሪዎች 26 የክልል-ደህንነት አስተባባሪዎች 6 በኤሌክትሮኒክስ የፍተሻ ሠራተኞች 7

5 ት/ቤቶችን በቴክኖሎጂ ጥበቃ ማድረግ የመግቢያ በሮች ቁጥጥር ሲስተም (ACS) ሁሉም የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይጠቀማሉ። እነዚህ ካሜራዎች ተቆጣጣሪ ግለሰቦች ጎብኚዎችን ወደ ት/ቤት ግቢ ከማስገባታቸው በፊት የጎብኚዎችን ማንነት ለማየት ይረዳሉ። የጎብኚዎች ማኔጅመንት ስልቶች (VMS) ት/ቤቶች የሚጠቀሙት ሁሉንም ጎብኚዎች የመንጃ ፈቃዳቸውን እያሳዩ እንዲፈርሙ እና ወዲያውኑ ከመንጃ ፈቃድ በተገኘ መረጃ በሜሪላንድ ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙ ሰዎችን ከመዝገብ በስማቸው ለመለየት ያስችላል።

6 የት/ቤትን ደህንነት በቴክኖሎጂ መጠበቅ
ከ 5,500 ካሜራዎች በላይ በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከውስጥ እና ከውጭ ዲጂታል ክትትል/ቁጥጥር ይደረጋል። በአማካይ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከ100 በላይ ካሜራዎች አላቸው እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች በአማካይ ከ70 እስከ 70 ካሜራዎች ለእያንዳንዳቸው ት/ቤት አሏቸው። ከ800 በላይ የት/ቤት አውቶቡሶች የተማሪዎችን እንቅስቃሴዎች ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የውስጥ ካሜራ አላቸው። ለት/ቤት አውቶቡሶች፣ ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አስተዳደር፣እና ለደህንነት ሠራተኞች ተንቀሳቃሽ ሬዲዮ ለመግዛት የመገናኛ ስልት መስመሮች ተዘርግተዋል።

7 አገልግሎቶች ህንፃ መቆጣጠሪያዎችን ማሻሻል የመማሪያ ክፍሎች መብራቶች ማሻሻል
የዋና መግቢያ፣ ኮርደር አካባቢ ፣ ከኮሪዶር መተላለፊያ ከብረት የተሰሩ በሮች ሁሉንም ጎብኚዎች መጀመሪያ ወደ ት/ቤት ሲገቡ በዋናው ቢሮ መግቢያ በኩል መግባት እንዲችሉ መምራት የመማሪያ ክፍሎች የመማሪያ ክፍሎችን በሮች መከላከያ ማጥበቅ መብራቶች ማሻሻል የሚጨመሩ እና የሚሻሻሉ FY19-24 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም(CIP) በጀት ወደ ት/ቤት መግቢያዎችን ለማሻሻል ከአነስተኞቹ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ $4.9 ሚሊዮን ተጨምሯል።

8 ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሰላማዊ የመማሪያ አካባቢ መስጠት
እያንዳንዱ የMCPS ት/ቤት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሰላማዊ የመማሪያ አካባቢ መስጠት ይጠበቅበታል። ደህንነትን በተመለከተ ነቅቶ ለመጠበቅና ከደህንነት ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን ለመጨመር ት/ቤቶች የወሰኗቸው አንዳንድ እርምጃዎች የሚያካትቱት፦ የደህንነት ጥበቃ ሠራተኞች ስምሪት ለሁሉም ሠራተኞች ግዴታ የሆነ ለድንገተኛ ሁኔታ ዝግጁነት ስልጠና ድንገተኛ ሁኔታን ለመቋቋም ልምምድ ማድረግ/Emergency drills ከውጭ ኤጀንሲዎች ጋር መሥራት የከሪኩለም ትምህርት በተማሪ የሥራ አገልግሎት አማካይነት የተማሪ እና የቤተሰብ ድጋፍ

9 ለሁሉም ሠራተኞች ግዴታ የሆነ ድንገተኛ ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችል ስልጠና
የደህንነት ሠራተኞች ስምሪት እያንዳንዱ የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የደህንነት ጥበቃ ጓድ መሪ እና በት/ቤቱ ስፋት እና በተማሪዎች ቁጥር እንዲሁም በፕሮግራሞች ፍላጎት ላይ በመመርኮዝ ከ4 እስከ 8 የደህንነት ጥበቃ ረዳቶች ተመድበውላቸዋል። የኤለመንተሪ ት/ቤቶች ከክልል/cluster የደህንነት ጥበቃ ጓድ፣ በክላስተር አስተባባሪዎች አማካይነት ከዋና ጽ/ቤት ሠራተኞች እና ከ SRO እንደየአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ድጋፍ ያገኛሉ። ለሁሉም ሠራተኞች ግዴታ የሆነ ድንገተኛ ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችል ስልጠና በት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚፈጠሩ ለድንገተኛ ሁኔታዎች እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ የት/ቤት ሠራተኞች በየዓመቱ ስልጠና ይሰጣቸዋል። ስለ አደንዛዥ እፆች፣ ቀውስ ሲፈጠር ጣልቃ ስለመግባት፣ ወሮበላ ውንብድናን መከላከል፣ ስለ ፍተሻ እና መውረስ፣ ስለ ተማሪ የአእምሮ ጤንነት፣ እና የዳበረ ባህልን በሚመለከት የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ሠራተኞች ተጨማሪ ስልጠና ያገኛሉ።

10 ድንገተኛ ሁኔታዎችን ለማምለጥ መለማመድ
የ MCPS ት/ቤቶች በሙሉ ቢያንስ ስድስት የድንገተኛ ሁኔታዎችን የመቋቋም/የማምለጥ ልምምድ በማድረግ መሣተፍ ይኖርባቸዋል። ይህ የሚያካትተው ከውስጥ መቆለፍ፣ መጠለያ ተገን ማድረግ፣ ጥሎ መውጣት፣ ሰላም መሆኑ ሲረጋገጥ መመለስ፣ አደገኛ የአየር ሁኔታ፣ እና ባሉበት ለጥ ብሎ መቆየት፤ ከእሳት አደጋ ለማምለጥ ልምምድ ማድረግም እንደዚሁ ግዴታ ነው። ከውጭ ኤጀንሲዎች ጋር አብሮ መሥራት እያንዳንዱ የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት - የት/ቤት ንብረት መኮንን/School Resource Officer (SRO) ተመድቦለታል። SRO ማለት ጤናማ አካባቢ ለመፍጠር ከተማሪዎች ጋር ግንኙነቶችን በመገንባት፣ ለድንገተኛ ሁኔታ በሚደረግ ዝግጅት በመርዳት፣ እና የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ህግን በማስፈጸም በቀጥታ ከት/ቤት ሠራተኞች ጋር የሚሠሩ ዩኒፎርም የለበሱ የፖሊስ መኮንኖች ናቸው። MCPS በካውንቲው ውስጥ ካሉት የህግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች (MOU) ጋር ትብብር የማድረግ ስምምነት አለው። SRO እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የደህንነት ጥበቃ ጓዶች ቀውስ በተፈጠረ ጊዜ ወይም አሳሳቢ ክስተት ሲኖር የኤለመንተሪ ት/ቤቶችን ለመርዳት ይችላሉ።

11 ከሪኩለም እና የማስተማር ፕሮግራም የጤና ትምህርት የሚሰጡ ሰባት ክፍሎች (ከአፀደ ህፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት) የአእምሮና የስሜት ጤንነት ግንኙነት፣ ራስን መምራት፣ ማቀንቀን ደህንነት እና ጉዳትን መከላከል የመጀመሪያ እርዳታ፣ CPR፣ የድንገተኛ ሁኔታ ምላሽ ስለጤንነት መሠረታዊ እውቀት ተፅዕኖዎችን መተንተን መረጃ/ኢንፎርሜሽን ማግኘት በሰዎች መካከል ግንኙነት ውሳኔ መስጠት ግብ/አላማ ይዞ መነሳት ራስን መምራት አቀንቃኝነት MCPS health education occurs from Pre-k through high school. In Grade 6 and 10, students receive instruction on First aid and emergency response and personal safety. In grade 8, SIP is focused on cyber safety and sexual harassment. In high school students receive kinesthetic (hands-on) instruction for CPR and AED use.

12 የተማሪ እና የቤተሰብ ድጋፍ አገልግሎቶች
ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦች የ MCPS መገልገያዎች/resources Office of Student and Family Support and Engagement website: የት/ቤት ካውንስሊንግ የስነልቦና/ሳይኮሎጂ አገልግሎቶች የቤተሰብ ተሳትፎ የአእምሮ ጤንነት እና ከፍተኛ ቀውስ/crisis ድጋፍ ስለ አደንዛዥ እፅ አጠቃቀም የማህበረሰብ መገልገያዎች/resources አወንታዊ ስነምግባራዊ ጣልቃ-ገብነቶችና ድጋፎች Positive Behavioral Interventions and Supports, ፍትሃዊ ተሃድሶ ዋልጌነት/ወስላታነት እና ትምህርት ማቋረጥን መከላከል የማህበረሰብ መገልገያዎች EveryMind Family Services, Inc./የቤተሰብ አገልግሎቶች ጥምረት የሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ የስነምግባር ደህንነት እና የቀውስ አገልግሎቶች ስለ ልጆች እና ወጣትነት ምልመላ እና ክትትል አገልግሎቶች (Screening and Assessment Services for Children and Adolescents የአውታረመረብ መገልገያዎች/Online resources National Association of School Psychologists PREPaRE Curriculum ( ቀውስን መከላከል እና ዝግጁነት ሁለገብ የት/ቤት ደህንነት እቅድ ስለቀውስ ጣልቃገብነት እና ማገገም/ተሀድሶ የት/ቤት የአእምሮ ጤና ባለሞያዎች ሚና

13 ከት/ቤት እስከ ዋናው ጽ/ቤት ግንኙነት
የት/ቤቶች ድጋፍ እና ማሻሻል ጽ/ቤት (OSSI) መደበኛ የት/ቤት ሥራ የሚያደናቅፍ ወይም በት/ቤት ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ ሁኔታዎችን መረጃ/ኢንፎርሜሽን ከት/ቤቶች ይደርሰዋል። OSSI በቅድሚያ ተዘጋጅቶ ባለው የዋና ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ዝርዝር መሠረት ከሥራ ሂደት እና ኮሙኒኬሽን ሠራተኞችን ጨምሮ የተገኙ መረጃዎችን/ኢንፎርሜሽን ያሠራጫል። አስጊ ክስተቶችን የመምራት ስልት ሁኔታዎች በሚከሰቱ ወቅት እና ከዚያም በኋላ ለማህበረሰቡ ይላካል። ለት/ቤት ማህበረሰብ ለማሳወቅ ርእሰመምህሩ ConnectED ወይም listserv መጠቀም ይችላል። በሰፊው የመገናኘት/የማሳወቁ ጉዳይ እንደክስተቱ ሁኔታ ይወሰናል።

14 የት/ቤት የግንኙነት ሥርአት ፕሮቶኮል
ድንገተኛ ሁኔታዎችን ለት/ቤት ማህበረሰብ ማስጠንቀቂያ መስጠት የድንገተኛ የአስቸኳይ ጊዜ እቅዳችን ማእከላዊ ነገር ነው። ስለት/ቤት ደህንነት አሳማኝ/ትክክለኛ የሆነ አስጊ ሁኔታ ካለ ወላጆች መውሰድ ስላለባቸው እርምጃ መረጃ/ኢንፎርሜሽን ለመስጠት ለቤተሰብ መልክት ይተላለፋል። የትምህርት ሂደትን የሚያደናቅፍ ዛቻ የተሳሳተ መረጃ ሲኖር ት/ቤቶች ለቤተሰቦች ያሳውቃሉ። ድንገተኛ መረጃ/ኢንፎርሜሽን ከ MCPS አካውንት ካልሆነ በስተቀር ከማህበራዊ ሚዲያ የሚሠራጭ ኢንፎርሜሽን ላይ አትደገፉ።

15 የት/ቤት ደህንነት ግምገማ የጊዜ ሠሌዳ
ስፕሪንግ 2017 የ MCPS የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ እና የንብረት ማኔጅመንት የትምህርት ቤት ደህንነት በተመለከተ ከሁለት በአገርአቀፍ ደርጃ የታወቁ አማካሪዎች/nationally recognized consultants ጋር በመተባበር በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ሁኔታ በጥልቀት ተገምግሟል። ሰመር 2017 በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ ያተኮረ የት/ቤት ደህንነት አስተያየት የተሰጠባቸው ቅድሚያ ትኩረት የሚደረግባቸው ሰባት ቁልፍ የሆኑ ነገሮችን ለማሻሻል MCPS ሪፖርት አስተላልፏል። ፎል 2017/ዊንተር 2018 የሁሉም የኤለመንተሪ እና የሚድል ስኩል MCPS ቡድን ተከታታይ ግምገማዎች

16 ጊዜያዊ ሪፖርት ሰባት ቁልፍ የሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎች
ስለ ት/ቤት ደህንነት እና መልካም የት/ቤት ባህል በመረጃ ላይ የተደገፈ ኃላፊነት/ተጠያቂነት የት/ቤት ደህንነት ጥበቃ ሠራተኞች እና ሌሎች ሠራተኞችን ውጤታማ ምደባ፣ አጠቃቀም፣ እና ማኔጅመንት የሰኩሪቲ ካሜራዎች፣ እና አጠቃቀማቸውን ጨምሮ ቴክኖሎጂ መዘርጋት ለብቻቸው የተለዩ ህንፃዎችንና የት/ቤት መገልገያዎችን መጫወቻ ሜዳዎችን መግቢያ ላይ ጥብቅ ማድረግ። የተማሪን መልካም ስነምግባር የመደገፍ ስርአትና አፈጻጸም ሥርአት አቀፍ የመከላከል እና ቅድሚያ ጣልቃ ገብ ፕሮግራሞች ከህግ አስከባሪዎች እና ሌሎችም አጋር ኤጀንሲዎች ጋር በትብብር መስራት

17 ከግምገማው የመነጨ የሥራ እቅድ የደህንነት ጥበቃ አሠራር ሞዴል፣ የሥራ መግለጫዎችን፣ ደረጃ የጠበቀ/መደበኛ የአሠራር ስልቶችን መገምገም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ ለማሳደስ እና ለማግኘት (ACS, VMS, cameras) ስልታዊ ዝግጅት እና የተባበረ ጥረት መቀጠል። አገልግሎት ለማቀላጠፍ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለማሟላት የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ወደ ት/ቤቶች መግቢያ በሮችን እና ሌሎች አነስተኛ ፕሮጀክቶችን ለመስራት $4.9 ሚሊዮን የተማሪ የአእምሮ ጤንነት ፕሮግራሞችን የተሃድሶ ተግባሮች፣ ቀዳሚ ጣልቃገብ ተግባር፣ እና መልካም ስነምግባርን ተግባራዊ ስልት/አፈጻጸም መቀጠል የማህበራዊ ሚዲያ ቁጥጥር ከት/ቤት ማህበረሰብ እና ከአጋር ኤጀንሲዎች ጋር ሥርአት አቀፍ ግልጽነት የተሞላበት ግንኙነት


Download ppt "የሞንጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ት/ቤት ደህንነት እና ሰላም የሚቀርብ ገለፃ"

Similar presentations


Ads by Google